የሐረሪ ክልላዊ መንግስት በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፍ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

87

ሐረር ፤ የካቲት 25 ቀን 2014(ኢዜአ) የሐረሪ ከልላዊ መንግስት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፍ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ።


የክልሉ መንግስት ባወጣው የሀዘን መግለጫ "በቅዱስነታቸው ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በክልሉ መንግስት ህዝብ ስም ይገልጻል" ብሏል።


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ የቤተክርስትያኗ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ዘግቧል።


ቅዱስነታቸው ሰሞኑን ባደረባቸው ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው መቆየቱ ይታወሳል።


የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ መግለጫ አውጥተዋል።


የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም