የንግድ ባንክ የ10ኛ ዙር ይቆጥቡ ይሸለሙ ዕጣ ወጣ

66

የካቲት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10ኛው ዙር የይቆጥቡ ይሸለሙ የዕጣ አወጣጥ መርኃ ግብር ተካሄደ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባንኩ ላለፉት 80 ዓመታት የኅብረተሰቡን ቁጠባ ባህል ለማዳበር የሚያስችሉ የተለያዩ የማበረታቻ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ከእነዚህም የማበረታቻ ተግባራት መካከል ይቆጥቡ ይሸለሙ መርኃ ግብር አንዱ መሆኑን አመልክተው፤ 72 ሽልማቶችን የያዘው 10ኛ ዙር ይቆጥቡ ይሸለሙ መርኃ ግብር ዛሬ መካሄዱን ተናግረዋል።

ሁለት የመኖሪያ አፓርትመንቶች፣ 10 ዘመናዊ አውቶሞቢሎች፣ 30 ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎችና 30 ላፕቶፖች በዕጣው ተካተዋል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የዕጣ አወጣጥ መርኃ ግብር በአንደኛ እጣ 2 የመኖሪያ አፓርትመንቶች 275600863928 እና 1188200154301 አሸናፊ ቁጥሮች ሆነዋል።

እንዲሁም 10 ዘመናዊ አውቶሞቢሎች አሸናፊ ቁጥሮች መካከል 356200510231 ይገኝበታል።

3ኛ እጣ 30 ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪዎችና አራተኛው 30 የላፕቶፖች አሸናፊ ቁጥሮች በተመሳሳይ ይፋ ሆኗል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም