ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ማረፍ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ማረፍ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የካቲት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ማረፍ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
"ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ አምላካቸው ሄደዋል፤ልባዊ ሃዘኔን ለቤተሰባቸውና ለመላ ኢትዮጵያውያን እገልጻለሁ፤ትላንት ሆስፒታል ስለነበርኩ ስለ ጤንነታቸው የሰማሁት አሳስቦኝ ነበር: ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን፤ በክብር እንሸኛቸው " ሲሉ ገልጸዋል ::