የኢዜአን የ80 ዓመት ጉዞ የሚዘክር የፎቶ አውደርዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በተገኙበት ተመርቆ ተከፈተ

193

የካቲት 25/2014/ኢዜአ/ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን (ኢዜአ) የ80 ዓመት ጉዞ የሚዘክር የፎቶ አውደርዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተመርቆ ተከፈተ።

የፎቶ ዓውደርዕዩን የመከላከያ ሚኒስትርና የኢዜአ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አብርሃም በላይ እና የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መርቀው ከፍተውታል።

May be an image of 5 people, people standing and outdoors

ተቋሙ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበር ጀምሯል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የኢዜአ ባለድርሻ አካላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

የፎቶ ዓውደርዕዩ ለሚቀጥሉት አስር ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።

ኢዜአ ዘንድሮ 80ኛ ዓመቱን የያዘ ሲሆን የምስረታ በአሉንም በፎቶ ዓውደርእይ፣ በፓናል ውይይት እና በሌሎችም መርሀግብሮች የሚያከብር ይሆናል።