ከንቲባ አዳነች አቤቤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

150

የካቲት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ በማረፋቸው ሀዘን እንደተሰማቸው ገለፁ።

በቅዱስነታቸው ዜና ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ገልፀዋል።

የቅዱስነታቸውን ነብስ ፈጣሪ በአፀደ ገነት ያኖረው ዘንድ እንደሚመኙም ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ጠቁመዋል።