ዩኒቨርሲቲዎች ብቁ ዜጋ የማፍራት ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

221

ጂንካ የካቲት 24/2014(ኢዜአ) ዩኒቨርሲቲዎች በእውቀት የካበተና ብቁ የሆነ ሀገር ተረካቢ ዜጋ በማፍራት ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ጥራት ችግሮችና  መፍትሄዎች  ላይ ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር እየተወያዩ ነው።

ሚኒስትሩ  በዚህ ወቅት እንዳሉት “የትምህርት ጥራት ማነስ ችግር አለ፤ ለዚህም ምክንያቶች አንዱ ባለፉት 27 ዓመታት በሥርዓተ ትምህርቱ ላይ የነበረው አሻጥር ነው” ።

ክፍተቶቹን በመሙላት  ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ብቁና በእውቀት የካበቱ መምህራንና አምራች ዜጎችን ለማፍራት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ተቋማቱ በተለይ ኩረጃን የሚፀየፍ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ድርሻቸውን በብቃትና በሃላፊነት ስሜት እንዲወጡ ፕሮፌሰር ብርሃኑ አሳስበዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ለሚያነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡና በመቀጠልም የተቋሙን  የመማር ማስተማርን ሥራን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።