በመከላከያ ህብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ በስራቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራርና አባላቱ የእውቅናና የምስጋና ዝግጅት በመካሄድ ላይ ነው

203

የካቲት 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የመከላከያ ህብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ በስራቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራርና አባላቱ የእውቅናና የምስጋና ዝግጅት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የዋና መምሪያው በስሩ ለሚገኙ ኮሌጆችና አካዳሚዎች በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላሳዩና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አባላት የሜዳይና የማዕረግ ዕድገት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰን ጨምሮን ሌሎ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም