የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻው በድል እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና ተሰጠ

97

አዲስ አበባ የካቲት 1/2014 /ኢዜአ / የመከላከያ ዋር ኮሌጅ የህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻው በድል እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋፅኦ ላደረጉ ግለሰቦችና ተቋማት ምስጋና እና እውቅና ሰጠ፡፡
የኮሌጁ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሃብታሙ ጥላሁን፤ በራሳቸው ተነሳሽነትና ፍላጎት አገራዊ ጥሪውን ተቀብለው የላቀ አበርክቶ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች ምስጋናና እውቅና መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

በዛሬው እለት አውቅና የተቸሩት ተቋማትና ግለሰቦች ኮሌጁን በሃሳብ፣ በገንዘብ፣ በአይነት፣ በጉልበት፣ በሙያና በሌሎችም መንገዶች ማገዛቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኮሌጁ የተደረገለት አበርክቶም ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ የላቀ ፋይዳ ነበረው ብለዋል፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ፤ ኢትዮጵያ በከሃዲዎች ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት "አገርን አስቀድማችሁ የተገኛችሁና የቻላችሁትን ሁሉ ድጋፍ ያደረጋችሁ ክብርና ምስጋና ይገባችኋል" ብለዋል፡፡

እውቅናው የተቸራቸው ግለሰቦችም ለኢትዮጵያ ህልውና ላደረግነው ሁሉ ክብርና ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

የኢትዮጵያን ህልውና ለማረጋገጥና አንድነቷን ለማስጠበቅ የሞራል ስንቅ ይሆናል፤ ድጋፋችንም ቀጣይነት ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

እውቅና ከተሰጣቸው መካከል አርቲስት ሀመልማል አባተ እኔ ላበረከትኩት አስተዋፅኦ ጥሪዬን ተቀብለው ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ አመሰግናለሁ ብላለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም