ባለፉት ስድስት ወራት ለብድር የወጣው 147 ቢሊዮን ብር ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

275

የካቲት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) “ባለፉት ስድስት ወራት ለብድር የወጣው 147 ቢሊዮን ብር ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ለብድር 147 ቢሊዮን ብር ወጪ መሆኑን ጠቅሰው፤ “ብድሩ በሴክተር ሲከፋፈል ለአገልግሎት 70 ቢሊዮን ብር፣ ለኢንዱስትሪ 50 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ለግብርና 27 ቢሊዮን ብር ብድር ወጥቷል” ብለዋል።

አገልግሎትና ኢንዱስትሪ ከግብርና ዘርፍ የበለጠ ሀብት መጠቀማቸው እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ቢሆን በግብርና ሴክተር የሚደረገው ኢንቨስትመንት በቂ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።