ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሐይል ማመንጨት ማብሰሪያ ሥነ -ሥርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር- - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሐይል ማመንጨት ማብሰሪያ ሥነ -ሥርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር-

አዲስ አበባ የካቲት 13/2014 (ኢዜአ) ቀዳማዊ አጼ ኃ/ሥላሴ በዘመናቸው ታላቁን ግድብ መገንባት የሚከብድ ቢሆንም የፕሮጀከቱ አስፈላጊነት ላይ ትልቅ ራዕይ በመሰነቃቸው ምስጋና አቀርባለሁ
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ፕሮጀክቱ እንዲጀመር በማድረጋቸው ምስጋና ይገባቸዋል
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምቹ ባልነበረው ፖለቲካዊ አውድ ውስጥ ሆነው የግድቡ ግንባታ እንዲቀጥል በማድረጋቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ
ሁሉም መሪዎች በተለያየ ጊዜና የፖለቲካ አመለካከት ላይ ቢኖሩም በኢትዮጵየዊነት መንፈስ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እውን እንዲሆን አንድ ሆነው ሰርተዋል
በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በአረቡ አለም በዲፕሎማሲው መስክ ከፍተኛ ተጋድሎያደረጉ ኢትዮጵያውያን ከፍ ያለ መስጋና አቀርባለሁ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይል ማመንጨት መጀመር ለሱዳንና ግብጽን ጨምሮ ለሁሉም እህትና ወንድም ህዝቦች የሚጠቅምኝ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ለማላት እፈልጋለሁ
ኢትዮጵያ ማንንም የመጉዳት ፍላጎት የላትም፤ ፍላጎቷም ኤሌክትሪክ አይተው የማያውቁ ዜጎቿን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ነው
ዛሬ ለኢትዮጵያ የብርሀን መባቻ ነውና መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን!