በአገራችን ጉዳይ ለመመካከር መዘጋጀታችን ለችግሮቻችን የጋራ መፍትሄ ማምጣት ያስችለናል

49

የካቲት 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአገራችን ጉዳይ ለመመካከር መዘጋጀታችን ለችግሮቻችን የጋራ መፍትሄ ማምጣት ያስችለናል ሲሉ የጥንት ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት ገልጹ፡፡

በኢትዮጵያ ዘመን እየተሻገሩ የመጡ ችግሮች የግጭትና የመገዳደል መዘዝ እያስከተሉ ይገኛሉ።

ለአገር አድገትና ብልፅግና ደግሞ የህዝቦች ሰላምና አብሮነት፣ የዴሞክራሲ መጎልበትና የፍትህ መስፈን ወሳኝነት አለው።

በኢትዮጵያ ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ ጥላቻን በፍቅር፤ ጸብን በእርቅ በመለወጥ አበሮነትን ማጠናከር ግድ ይላል።

ለዚህም ነው በኢትዮጵያ አካታችና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚል አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአዋጅ የተቃቋመው።

የአገራዊ ምክክሩም ዓላማ መሰረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ በመወያየት ቅራኔዎችንና ልዩነቶችን በማጥበብ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማምጣት ይሆናል።

ለዚህ መልካም ዓላማ ላነገበ ጉዳይ ሁላችንም ባለቤት በመሆናችን በአገራችን ጉዳይ ተመካክረን ልንግባባ ይገባል ይላሉ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ አባት አርበኞች።

በአገራችን ጉዳይ ለመመካከር መዘጋጀታችን ደግሞ ለችግሮች የጋራ መፍትሄ ለማምጣት ያስችለናል ነው ያሉት።

ለውይይቱ ስኬትና ውጤታማነት በተለይም ምሁራን፣ ሚዲያው፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አካታችና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚል በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም