በሀገራዊ የምክክር ጉዳይ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው

67

የካቲት12 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሀገራዊ የምክክር ጉዳይ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

"ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት ለሀገራዊ መግባባትና ለዘላቂ ሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ ነው መድረኩ እየተካሄደ ያለው።

በውይይት መድረኩ ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርና በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ ሁሉን አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ መሠረታዊነት ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምሁራን ለውይይት የሚሆኑ ፅሁፍ አቅርበው ምክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና ሌሎችም የድሬዳዋ ነዋሪዎች በውይይት መድረኩ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢዜአ ከሥፍራው ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም