የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሁለቱ የባሌ ዞኖች የድርቅ ተጎጂዎች ድጋፍ አደረገ

105

ጎባ ፤ የካቲት 11/2014(ኢዜአ). የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሁለቱ የባሌ ዞኖች የድርቅ ተጎጂ ወገኖች 78 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን በባሌ ሮቤ ተገኝተው ያስረከቡት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ናቸው።

ከንቲባዋ ድጋፉን ሲያስረክቡ ባስተላለፉት መልዕክት ድጋፉ የኢትዮጵያዊያን በችግር ጊዜ የመረዳዳት የቆየ ባህል ነው" ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለወደፊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሐኪም አልዩ ፤ ለተደረገው ድጋፍ  አመስግነው ፤ ከችግሩ ስፋት አንጻር ሌሎች ግለሰቦችና ተቋማትም መሰል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ከዋና አስተዳዳሪው ጋር ድጋፉን የተረከቡት የባሌ አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች ለከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ  ያላቸውን አክብሮት በመግለጽ መርቀው ሸኝተዋቸዋል።  

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪም  ለከንቲባዋ የባሌ ዞን የቱሪዝም መስህብ የሆነውን የሶፍ ኡመር ዋሻን ምስል በስጦታ አበርክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም