በተሽከርካሪ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

80

ዲላ የካቲት 10/2014 (ኢዜአ) በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ18 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አሰታወቀ።
የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አደጋው የደረሰው ዛሬ ከረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ በይርጋጨፌ ወረዳ ቆንጋ ቀበሌ ውስጥ  ነው።

65 ሰዎችን አሳፍሮ መነሻውን ከያቤሎ ከተማ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሴሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-34983 ኦሮ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው አደጋው የደረሰው።

በአደጋው በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሦስት ሰዎች እና ተሽከርካሪው ሲገለበጥ በአካባቢው  ሲጫወቱ የነበሩ ሦስት የአንድ ቤተሰብ አባላት  ሕይወት ማለፉን አስታውቀዋል።

በሌሎች በ13 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በአምስት ሰዎች ላይ ደግፎ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው  በይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ እና በዲላ ሪፈራል ሆስፒታሎች የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ረዳት ኢንስፔክተር  ታምራት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም