በቤትኪንግ የኢትዮጵያ የፕሪሚሪ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀድያ ሆሳዕና የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል

171

አዲስ አበባ የካቲት 10/2014 /ኢዜአ/ በ13ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ የፕሪሚሪ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀድያ ሆሳዕና የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ነጥብ ሊጉን እየመራ ሲሆን ሀዲያ ሆስአና ደግሞ በ22 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በዚህ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካሸነፈ ነጥቡን 29 በማድረስ መሪነቱ የሚያጠናክር ሲሆን ሀድያ ሆሳዕና ካሸነፈ ደግም በ25 ነጥብ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ይላል።

ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለውን የነጥብ ልዩነትም ከአራት ወደ አንድ የሚያጠብ ይሆናል።

በድሬዳዋ ከተማ እየተከናወነ ባለው መርሃ ግብር የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ ዛሬ ቀን 10፡00 ላይ ይካሄዳል።

ከዚህ ጨዋታ ቀጥሎ ምሽት 1፡00 አዳማ ከተማ ከመከላከያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ የፕሪሚሪሊግ ትናንት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገው አርባምንጭ ከተማ ኢትዮጵያን ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ድሬድዋ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም