ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ስደተኞችን በተመለከተ ከለጋሾች ቡድን ጋር ተወያዩ

170

የካቲት 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ስደተኞች ድጋፍ ስለሚያገኙበትና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ከለጋሽ ቡድን ጋር ተወያዩ።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ለስደተኞች ድጋፍ የሚያደርጉ የለጋሾች ቡድንን ተቀብለው ማነጋገራቸውን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ገልጿል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከለጋሾች ጋር በነበራቸው ቆይታም ለስደተኞች በሚያስፈልጉ ነገሮች፣ ለጋሾቹ በክልሉ ለሚገኙ ስደተኞች ድጋፍ ስለሚሰጡበት ሁኔታና አስፈላጊ እገዛዎችን ስለሚያደርጉበት ጉዳዮች መነጋገራቸው ተነግሯል።

የለጋሽ ቡድኑ በጋምቤላ በሚኖረው ቆይታ በመጠለያዎች ውስጥ ከሚገኙ ስደተኞችና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋርም ይወያያል ተብሏል።

በተጨማሪም ለጋሾች በሚያደርጉት ድጋፍ የተገኙ ለውጦችን በቆይታቸው እንደሚመለከቱ ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️