በአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴያችን በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የአፈር መሸርሸርን በስኬታማነት ለማስቀረት ተችሏል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

63

የካቲት 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) “በአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴያችን በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የአፈር መሸርሸርን በስኬታማነት ለማስቀረት ተችሏል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር አንዱ ዓላማው የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ የግብርናን ምርታማነት ማሻሻል፣ በረሀማነትና መዘዞቹን መከላከል እና ግድቦችን በደለል ከመሞላት መታደግ እንደሆነ ገልጸዋል።

“በአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴያችን በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የአፈር መሸርሸርን በስኬታማነት ለማስቀረት ተችሏል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በተባበረ ክንድ ኢትዮጵያችንን ልምላሜ ማልበሳችን ይቀጥላል!” ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው አስነብበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም