በሀገር መከላከያ ሠራዊት ደቡብ ዕዝ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ማልበስ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

140

ሀዋሳ የካቲት 6/2014 (ኢዜአ).. በሀገር መከላከያ ሠራዊት ደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የቆይታ ግዜያቸውን ላጠናቀቁ የሠራዊት አባላት የሜዳሊያ የማዕረግ ማልበስ እና ሽልማት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

የማዕረግ አሰጣጡ ሥነ-ስርዓት በመከላከያ ሰራዊት የብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ኢተፋ ራጋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በተገኙበት እየተከናወነ ነው።

የማዕረግ እድገቱ እየተሰጠ ያለው በዕዙ የላቀ የግዳጅ እፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የቆይታ ግዜያቸውን ላጠናቀቁ  የሠራዊት አባላት እንደሆነ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

የማዕረግ ዕድገቱ የባለ ሌላ ማዕረግ፥ መስመራዊ መኮንን እና ከፍተኛ መኮንን እንደሚያካትት ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።

የማዕረግ አሰጣጥ ሥነ-ስርዓቱ ለ33 የዕዙ አባላት ከምክትል አስር አለቃ እስከ ሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ የማልበስ ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም