39ኛው የጃንሜዳና 1ኛው የምሥራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውድድር በጃንሜዳ እየተካሄደ ነው

217

የካቲት 06 ቀን 2014 (ኢዜአ) 39ኛው የጃንሜዳና 1ኛው የምሥራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውድድር በጃንሜዳ እየተካሄደ ነው።

ከሩጫው መጀመር ቀደም ብሎ በኢፌዴሪ ባህልና ስፓርት ሚኒስትር የተዘጋጀው የማህበረሰብ አቀፉ የጤናና አካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተካሂዷል።

በጃንሜዳ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት እንቅስቃሴ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳም በሩጫ ውድድሩ ላይ ተገኝተዋል።