የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጋምቤላ ከተማ የኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊያስገነባ ነው

79

ጋምቤላ የካቲት 4/2014(ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጋምቤላ ከተማ በ79 ሚሊዮን ብር ለሚያስገነባው የኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ናቸው።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በስምንት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተመላክቷል።

ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወቅቱ እንዳሉት ትምህርት ቤቱን መገንባት ያስፈለገው  የሁለቱ ክልሎች ህዝቦችን በትምህርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው።

በኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች መካከል ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ በልማት የሚደረግ ትብብር እየተጠናከረ መጥቷል" ያሉት ደግሞ የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል በጋምቤላ ከተማ ለሚያስገነባው ትምህርት ቤት ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም