10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ ነገ እንደሚጀመር ድርጅቱ አስታወቀ

94

የካቲት 3 ቀን 2014 (ኢዜአ)10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ በነገው እለት እንደሚጀመር የበጎ ሰው ሽልማት በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ።

ድርጅቱ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ የእጩዎች ጥቆማ ነገ ይጀመራል።

ባለፉት አስርት ዓመታትም ለኢትዮጵያ በጎ የዋሉና ያሰቡ ኢትዮጵያዊያን በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ሲሰጥ መቆየቱ ተመላክቷል።

አርቲስት ሰርጸ ፍሬስብኃት የበጎ ሰው ሽልማት የአስር አመታት ሂደት በአዎንታዊ እና በአሉታዊ የተስተዋሉ ጉዳዮችን በመዳሰስ መልኩ የሚዘክሩ ጉዳዮች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል።

የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማም ከነገ አርብ እስከ መጋቢት 03/2014 ዓ/ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ለአንድ ወር እንደሚቆይ ገልጸዋል።

የእውቅና ሽልማቶቹ በ10 ዘርፎች የሚሰጡ ሲሆን በመምህርነት፣ በሳይንስ፣በኪነጥበብ፣ ፊልም ዳይሬክቲንግ፣ በበጎ አድራጎት፣ ቢዝነስና ስራ ፈጠራ፣ ቅርስ ጥበቃ እና ባህላዊ ጥናት፣በማህበራዊ ጥናት፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነት፣ መንግስታዊ ተቋማት እና ለኢትዮጵያ እድገት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ኢትዮጵያዊያን ይገኙበታል ብለዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም