ረጅሙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ በመጪው እሁድ ይመረቃል

108

የካቲት 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው ረጅሙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ በመጪው እሁድ እንደሚመረቅ ባንኩ አስታወቀ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና የአዲሱን ዋና መስሪያ ቤት ምርቃት ስነ-ስርዓትን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ድምቀት የሆነው 209 ሜትር ርዝመት ያለው በ165 ሺህ ሜትር ካሬ ቦታ ላይ ያረፈው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ባንኩ የደረሰበትን ከፍታ እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

ህንጻው ከመሬት በታች ያሉትን ጨምሮ 55 ወለሎች አሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም