በናይጄሪያው ግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር የተመራ የልዑካን ቡድን የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየጎበኘ ነው

71

ሐዋሳ የካቲት 1/2014 በናይጄሪያው ግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር በዶክተር ሞሀመድ ማህሙድ አቡበከር የተመራ የልዑካን ቡድን የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየጎበኘ ነው ።

በጉብኝቱ ላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በኢትዮጵያ የናይጄሪያ አምባሳደር ቪክቶር አዲኩንሌ እንዲሁም በናይጄሪያ የተለያዩ ክልል አስተዳዳሪዎችናእንግዶች ተገኝተዋል ።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተቀናጀ የግብርና አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዳይሬክተር አቶ አያልነህ አባዋ ፣የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አራርሶ ገረመውና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮችም በጉብኝቱ  ተገኝተዋል ።

ለልዑካን ቡድኑ ስለ ፓረኩ አጠቃላይ ገፅጻና ማብራሪያ እየቀረበ ነው።

ጉብኝቱ በኢትዮጵያና በናይጄሪያ በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ የልምድ ልውጥና የሁለትዮሽ ትስስርን ማጠናከር አላማ ያደረገ መሆኑ ታውቃል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም