በሽብርና ግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ከጦር መሣሪያዎች ጋር በቁጥጥር ሥር ዋሉ

104

ሚዛን፣ ጥር 25/2014 (ኢዜአ).በሽብርና ግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ከጦር መሣሪያዎች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በተደረገ ክትትል  ነው።

ከግለሰቦቹ መካከል ሁለት ከጅማ ፣ ሌሎች ሁለቱ ከቴፒና እንዲሁም አንዱ ከሚዛን ከተሞች መያዛቸውን ተናግረዋል ።

ግለሰቦቹለዘረፋና ግድያ ይጠቀሟቸው ከነበሩ አራት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ አንድ የእጅ ቦምብና ከወታደራዊ ትጥቆች ጋር መያዛቸውን አመልክተዋል።

እንዲሁም ሁለት ሽጉጦች፣ 279 የክላሽ ጥይቶችና የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አልባሳት ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ  ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በሕግ ጥላ ሥራ ሆነው ምርመራ እየተካሄደባቸው  መሆኑን አስታውቀዋል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉትግለሰቦች በተለይ  በቴፒ ከተማ ሲከሰት ለቆየው ግድያና ዘረፋ መሪ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩና ክትትል ሲደረግባቸው የቆዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የቴፒ ከተማ በወንጀለኞች ከሦስት ዓመት በላይ ሰላሟን አጥታ እንደቆየች ገልጸው ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እየተከናወኑ ባሉትተግባራት አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን አስረድተዋል።

ካለ ህዝቡ ጠንካራ ተሳትፎ ሰላምና ደህንነትን ማስፈንና ማረጋገጥ እንደማይቻል የተናገሩት ኃላፊው፣ ህብረተሰቡ  ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም