በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተመራ ልኡክ ጅግጅጋ ከተማ ገባ

112

አዲስ አበባ ጥር 25/2014(ኢዜአ) በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተመራ ልኡክ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ጅግጅጋ ከተማ ገባ።

የልኡክ ቡድኑ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ አቀባበል አድርገዋል።

May be an image of 9 people, people standing and outdoors

ልኡኩ ወደ ስፍራው ያቀናው በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል።

የአማራ ክልል፤ በኦሮሚያ ክልል ጎጂና ቦረና አካባቢዎች በድርቅ ለደረሰው ጉዳት በትናንትናው እለት የእንስሳት መኖ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም