የኢትዮጵያ የውጭ ቦንድ ሽያጭ ከፍተኛ መሻሻል አሳየ

125

ጥር 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአለም ላይ ቦንድ ለሽያጭ ካቀረቡ ሀገራት መካከል የኢትዮጵያ የውጭ ቦንድ ሽያጭ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱ ተገለጸ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በአገሪቱ ያለው የጸጥታ ችግር መርገቡን መግለጹን ተከትሎ የቦንድ ሽያጩ በዶላር 6 ሳንቲም የፍላጎት ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው።

የቦንድ ሽያጩ በ13 በመቶ የአፈጻጸም ዕድገት ማሳየቱ ከ80 በማደግ ላይ ካሉ አገሮች አንጻር የተሻለ መሆኑን ብሉምበርግ ገልጿል።

ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በጸጥታ ችግር ምክንያት የቦንድ ሽያጩ ቀንሶ እንደነበርም አስታውሷል።

ለዚህ እንደምክንያት የቀረበውም ተጥሎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ነው ተብሏል።

የውጭ ቦንድ በዓለም ላይ ፍላጎት ላላቸው ተቋማት ከኢትዮጵያ ቦንድ እንዲገዙ በምትኩ ኢትዮጵያ ወለድ አስባ የምትከፍላቸው ሰነድ ሲሆን ቦንዱ ለሽያጭ የሚቀርበው የውጪ ምንዛሬ ክፍተትን ለመሙላት፣ የቆዩ የውጪ እዳዎችን በአፋጣኝ ለመክፈል፣ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም