የካሜሩን፣ የቻድ፣ የኮትዲቭዋር፣ የኮንጎና የአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

214

ጥር 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) በ40ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ለመሳተፍ የካሜሩን፣ የቻድ፣ የኮትዲቭዋር፣ የኮንጎና የአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ።

የካሜሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጄኡን ምቤላ ምቤላ፣ የቻድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሃማት ዜኔ ቸሪፍ፣ የኮትዲቭዋር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንዲያ ካሚሶኮ ካማራ፣ የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂን-ክላውድ ጋኮሶ እንዲሁም የአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስሜራልድ ሜንዶንካ ቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ዋና ሹም አምባሳደር ፈይሰል አሊ ተቀብለዋቸዋል።