የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ጉዳት የደረሠባቸውን ትምህርት ቤቶች ሊገነባ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ጉዳት የደረሠባቸውን ትምህርት ቤቶች ሊገነባ ነው

ጥር 20 ቀን 2014 (ኢዜአ)የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ጉዳት የደረሠባቸውን ትምህርት ቤቶች ለመገንባት ቃል መግባቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንዳሉት፤የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በክልሎቹ ጉዳት የደረሰባቸውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በተሻለ መልኩ ለመገንባት ቃል ገብቷል።
ትረስት ፈንዱ ለትምህርት ቤቶቹ ግንባታ 3 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያደርግና ግንባታውም ከዘጠኝ ወር እስከ አንድ ዓመት ጊዜ ይወስዳል ተብሎ እንደሚገመት ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ በተሻለ ጥራትና ደረጃ እንደሚገነቡ ገልጸው፤ይህም የትምህርት ጥራትን ለማስፈን የጎላ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
