ፈረንሳይ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አደረገች

149

ጥር 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) ፈረንሳይ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ለኢትዮጵያ አድርጋለች፡፡

ድጋፉን ኢትዮጵያ በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት በተያዘው ሳምንት መረከቧ ታውቋል፡፡

ድጋፉ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ከፈረንሳይ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ያገኘች ቀዳሚ አገር እንደሚያደርጋት በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡