የሐረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት የመወያያ አጀንዳዎች ባለመቅረባቸው ጉባኤውን በወቅቱ ማካሄድ እንዳልቻለ አስታወቀ

52
ሐረር ነሃሴ 24/2010 የሐረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 3ኛ ዙር 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን የመወያያ አጀንዳዎች ባለመቅረባቸው በወቅቱ ማካሄድ አለመቻሉን አስታወቀ። የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አብዱልማሊክ በከር ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት የክልሉ ምክር ቤት ነሐሴ 23 ቀን ያካሂድ የነበረውን መደበኛ ጉባኤ ወደ ነሐሴ 24 ቀን 2010 አራዝሞ ነበር። በሁለቱ ቀናት ለክልሉ ምክር ቤት የሚቀርቡት የ2010 የመስተዳድሩ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ2011 የስራ እቅድ፣ ረቂቅ የበጀት አዋጅ እና ሌሎች አጀንዳዎች ባለመቅረባቸው ጉባኤው ሳይካሄድ ቀርቷል። ምክር ቤቱ የየዘርፉ አጀንዳዎች  እንደደረሱት ጉባዔውን የሚያካሂድ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም