ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

167

ሐረር፣ ጥር 18 /2014 (ኢዜአ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ከተማ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለኢዜአ እንደገለጹት መነሻውን ሶማሌ ላንድ ያደረገው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -06025 ሱማ የጭነት ተሽከርካሪ ጨለማን ተገን አድርጎ ከሶማሌ ክልል ፊቅ ዞን ወደ መሃል አገር የኮንትሮባንድ እቃ ሊያስገባ ሲሞክር በዞኑ ባቢሌ ከተማ የፍተሻ ኬላ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የኮንትሮባንድ እቃው በጸጥታ ሀይሎች ቅንጅት በኬላ ፍተሻ መያዙን ተናግረዋል ።

ከኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ጨርቃጨርቅ ፣ኤሌክትሮኒክስ ፣ልባሽ ጨርቆች ፣ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ፣የተሽከርካሪ ጎማ፣ የአዋቂና የህጻናት ጫማዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል ።

ኮንትሮባንድ እቃውን ሲያጓጉዝ የነበረ አሽከርካሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ አስታውቀዋል።