ንብረትነቱ የመከላከያ ሰራዊት የሆነ አውሮፕላን ተከስክሶ 17 ሰዎች ሞቱ

112
አዳማ ነሃሴ 24/2010 ንብረትነቱ የመከላከያ ሰራዊት የሆነ ዳሽ ሲክስ የተባለ አውሮፕላን ከድሬዳዋ ወደ ቢሾፍቱ 17 ሰዎችን አሳፍሮ በመብረር ላይ እንዳለ ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ናናዋ ቀበሌ አካባቢ በመከስከሱ በውስጡ የነበሩ ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው አለፈ። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ እንደገለጹት ልዩ ስፍራው ቦሩ ቢቲዳሊ በተባለ ቦታ ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 በተከሰከሰው አውሮፕላን ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ ሁለት ህጻናትና ሁለት ሴቶች ይገኙበታል። ከሞጆ ከተማ በቅርብ እርቀት በወደቀው አውሮፕላን የሞቱትን ሶስቱን የአውሮፕላኑን አብራሪዎች ጨምሮ የማቾችን አስከሬን በሁለት ሔሊኮፕተር በመታገዝ ከስፍራው እየተነሳ መሆኑን ገልጸዋል አውሮፕላኑ ሲወድቅም ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቀጣጥሎ እንደነበረና የአደጋው ዝርዝር ሁኔታ እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም