አሸባሪው ህወሓት ንብረትነቱ የ21 ሺህ አርሶ አደሮች የሆነውን የዋቢ ዩኒየን መጋዘንን ዘርፏል

68

የዩኒየኑ መገልገያ የነበረውን አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪን ጨምሮ የምስር፣ አተርና ባቄላ መከኪያ ማሽን በሽብር ቡድኑ ዘርፎ ወስዷል ብለዋል።

በመጋዘኑ ለአርሶ አደሮችና ለማህበረሰቡ ሊከፋፈሉ የነበሩ የአፈር ማዳበሪያ፣ ስኳርና ሸቀጣ ሸቀጥ በሙሉ በሽብር ቡድኑ መዘረፋቸውን ገልጸዋል።

ከዚህም ባሻገር የተለያዩ የወጭና የገቢ  ሰነዶችን ቀዳዶ በመጣል ከጥቅም ውጭ ማድረጉንም ስራ አስኪያጁ አስረድተዋል።

አሸባሪው ህወሓት የፈጸመው እኩይ ድርጊት ለሕዝብ ያለውን ጥላቻና የክፋት ጥጉ እስከምን ድረስ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዞኑ የህብረት ስራ ማህበራት ፅህፈት ቤት የግብይት ቡድን መሪ አቶ ግርማ ሞገስ በበኩላቸው ዩኒየኑን መልሶ ወደ ስራ ለማስገባት ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

ዩኒዩኑ የተለያዩ ሸቀጦችን ለህብረተሰቡ በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ተግባሩን ለማስቀጠል ከሌሎች ዩኒየኖች ጋር ትስስር በመፍጠር ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ አመልክተዋል።

የሽብር ቡድኑ ከዩኒየኑ በተጨማሪ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ያሉ የመሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራትን ንብረቶች መዝረፉንም አቶ ግርማ ተናግረዋል።

የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ስራ ዩኒዮን 56 ህብረት ስራ ማህበራትን አቅፎ የገበያ ማረጋጋትና የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የግብርና ግብዓቶችን ሲያቀርብ መቆየቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም