በሀገር መከላከያ የሰባተኛ ዕዝ ጀብድ ለፈፀሙ የሠራዊቱ አመራሮችና መኮንኖች እውቅና ሰጠ

329

ጥር 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢፌዴሪ የአገር መከላከያ ሠራዊት የሰባተኛ ዕዝ ጀብድ ለፈፀሙ የሠራዊት አመራሮችና መኮንኖች ሽልማትና ዕውቅና ሰጠ።

በዕውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ ሥነስርዓቱ ላይ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ጀብድ የፈጸሙ የሠራዊት አባላትን ማበረታት ለቀጣይ ተልዕኮ ያዘጋጃል።

በዕዙ ምርጥ አዋጊ፣ ተዋጊና አገልግሎ ሰጭ የሠራዊት አባላትና አመራሮች ዕውቅና እና ሽልማት መስጠቱ የሀገር ኩራት መሆኑንም ገልጸዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአባቶቹ የተረከበውን የሀገር ነፃነት ለማስከበር የሚከፍለው መስዋዕትነት በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ክብር ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ብለዋል።

ከፍተኛ አመራሮቹ እንዳሉት፤ አሸባሪው ህወሓት ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የያዘው ግብ በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት በመክሸፉ ሀገር ተከብራ እንድትኖር አድርጓል።

በሽብር ቡድኑ ላይ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በወሰዱበት እርምጃም ግፍና በደል ይፈፀምባቸው የነበሩ ዜጎችን ነፃ ማውጣት ተችሏል ብለዋል።

በሥነሥርዓቱ ላይ “ትጥቃችንን ሳናላላ ኢትዮጵያን በጀግንነት እንጠብቃለን!”፤ “በተሰጠን ሽልማት ሳንኩራራ የላቀ ስራ ለመፈፀም ሁሌም እንተጋለን”! የሚሉና ሌሎች ተያየዥ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

በህዳር ወር 2014 ዓ.ም መጀመሪያ የተመሰረተው ዕዙ አሸባሪው ህወሓትን ለመደምሰስ በተካሄዱ አውደ ውጊያዎች አኩሪ ተጋድሎ መፈጸሙ በሥነሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼