የደቡብ ክልል ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

144

አርባ ምንጭ (ኢዜአ) ጥር 15/2014---የደቡብ ክልል ስፖርት ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ እየተካሄደ ነው።

በአርባ ምንጭ ኃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ባለው ጉባኤ "ስፖርትን ለማህበራዊ ልማት መሳሪያነት በመጠቀም የህብረተሰቡን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ሃሳብ ነው።

በጉባኤው የክልሉ ስፖርት ፍኖተ ካርታን ጨምሮ የተለያዩ ረቂቅ መመሪያዎች ቀርበው ውይይት ከተካሄደባቸው በኋላ በምክር ቤቱ እንደሚጸድቁ ይጠበቃል።

የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እቶ ተስፋዬ ብላቱ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ከመመሪያዎች ውስጥ የክልሉ የስፖርት ምክር ቤት ማቋቋሚያና መተዳደሪያ ደንብ ይገኝበታል።

ዛሬ በሚጠናቀቀው ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የስፖርት ምክር ቤቱ ስብሳቢ እቶ ርስቱ ይርዳው የሙያ ማህበራት፣ የስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቶች፣ የምክር ቤቱ አባላት፣ ታዋቂ ባለሀብቶችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸው ታውቋል።

እቶ ርስቱ ይርዳው በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ቀጣይ የሥራ መመሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም