በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ ውድድር በወንዶች ገመቹ ዲዳ፤ በሴቶች ያለምዘርፍ የኋላው አሸነፉ

90

ጥር 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ ውድድር በወንዶች አትሌት ገመቹ ዲዳ፤ በሴቶች አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸነፉ።

በ2014 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተደረገው ውድድር በወንዶች አትሌት ገመቹ ዲዳ 1ኛ፣ አትሌት ጌታነህ ሞላ 2ኛ እንዲሁም አትሌት ቦኪ ድሪባ 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በሴቶች ደግሞ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 1ኛ፣ አትሌት ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር 2ኛ እንዲሁም አትሌት መልክናት ውዱ 3ኛ ደረጃን ይዘው ነው ያጠናቀቁት።

May be an image of 7 people and people standing

ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት ሲካሄድ የቆየ እና በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የስፖርት ፌስቲቫል ነው።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ሲሆን ከኢትዮጵያውን ባሻገር ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ የውጪ አገራት ዜጎች የሚሳተፉበት መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም