በደቡብ ክልል በተከናወኑ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎች ለውጥ ተመዝግቧል

57

ኮንሶ፤ ጥር 14/2014 (ኢዜአ) በደቡብ ክልል ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ እንክብካቤና ልማት ሥራዎች ለውጥ መመዝገባቸው ተገለጸ።

በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ስሩር እንደተናገሩት በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ እንክብካቤና ልማት ሥራዎች ለውጥ ተመዘግቧል።

በክልሉ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ  በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ዙሪያ ሶርቦ ቀበሌ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

አቶ ዑስማን በወቅቱ እንዳሉት፤ ለግብርና ምርት እድገት፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የህብረተሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተፋሰስ ልማት ወሳኝነት አለው።

በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፣ እንክብካቤና ልማት ሥራዎች ለውጥ ተመዝግቧል ብለዋል።

የአፈር ለምነትና እርጥበት ከመጨመሩና ደርቀው የነበሩ ምንጮች መመለስ ከመቻሉም ሌላ ተመናምኖ የነበሩ የግጦሽ ስፍራዎችና የተፈጥሮ ደን በማቆጥቆጥ ፍሬያማ ውጤት መገኘቱን አቶ ዑስማን አስታውቀዋል።

ዘንድሮ በየደረጃው በሚከናወነው ንቅናቄ  ከአዳዲስ ሥራዎች ባሻገር ነባር ተፋሰሶችን መጠገንና መንከባከብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በዚህ የልማት ስራ የአርሶና አርብቶ አደሮች፣ የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ ተመልክቷል።

በኮንሶ ዞን በተጀመረው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ ሥራ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳውና የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም