የአደባባይ በዓላት የኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ነፀብራቅ ናቸው

216

ሚዛን፣ ጥር 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጥምቀት በዓልን ጨምሮ ሌሎች የአደባባይ በዓላት የኢትዮጵያን አንድነት ለማጠናከር ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ በዓላቱ ከሃይማኖታዊ ይዘታቸው ባሻገር፤ ባህላዊና ትውፊታዊ እሴቶች እንዳይበረዙ መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።

የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፤ የዓለም ቅርስ  ሆኖ የተመዘገበው ጥምቀትና ሌሎች የአደባባይ በዓላት የአገራዊ አንድነት ነጸብራቅ እንደሆኑ አመልክተዋል።

የአደባባይ በዓላት የተለያዩ አካላትን የሚያሳትፉ በመሆናቸው የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንደሚያሳዩም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እሴት የሚንጸባረቁባቸው በዓላትም እንዳይበረዙ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም አስገንዝዋል።

በተለይ ወጣቶች ባህላዊና ሃይማኖታዊ ይዘቶችን ሳይቀላቅሉ ከአባቶች የተረከቡትን የአከባበር ሥርዓት ጠብቀው ለቀጣይ ትውልድ እንዲያስተላልፉ ጠይቀዋል ።

የአደባባይ በዓላት ኢትዮጵያዊ አንድነትን ከማጉላት ባለፈ ቱሪስቶችን በመሳብ የኢኮኖሚ ምንጭ ሆነው ስለሚያገለግሉም መጠበቅ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ጎብኚዎች የአደባባይ በዓላትን ለማየት ሲመጡ ቱባ ይዘታቸውን ለማየት በመሆኑ ከሃይማኖታዊ፣ ትውፊታዊና ባህላዊ ክዋኔዎች ውጭ የሚበርዙ ድርጊቶችን መጨመር ተገቢ አለመሆኑን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼