ዳያስፖራዎችና ከአገር ውስጥ ክለቦች የተውጣጣ ቡድን ለተፈናቀሉ ዜጎች የገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ኳስ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

94

ጥር 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) ዳያስፖራዎችና ከአገር ውስጥ ክለቦች የተውጣጣ ቡድን ለተፈናቀሉ ዜጎች የገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ኳስ ጨዋታ በመጪው እሁድ ጥር 15 ቀን 2014 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያደርጋሉ።

ጨዋታውን ለመመልከት ለዳያስፖራው በተለያየ ደረጃ የ50፣ 75 እና 100 ዶላር እንዲሁም ለአገር ውስጥ ተመልካቾች የነዋሪነት መታወቂያን መሰረት በማድረግ የ100፣ 500 እና የአንድ ሺህ ብር የመግቢያ ትኬቶች መዘጋጀታቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታውቋል።

የመግቢያ ትኬቱን በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ የበይን መረብ የገንዘብ ክፍያ አማራጭና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፍ ቢሮዎች መግዛት እንደሚቻል ገልጿል።

ዳያስፖራዎችና ከአገር ውስጥ ክለቦች የተውጣጣ ቡድን የሚያደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የአንድ ሚሊዮን ዳያስፖራዎች የአገር ቤት ጉዞ ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከተዘጋጁ መርሃ ግብሮች ውስጥ አንዱ ነው።

ጥር 8 ቀን 2014 ዓ.ም በታላቁ ቤተ-መንግስት ለተፈናቀሉ ዜጎች በተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት መርሃ ግብር በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ የበይን መረብ የገንዘብ ክፍያ አማራጭ አማካኝነት በተደረገ የትኬት ሽያጭ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም