ክልሉ በድርቅ ለተጎዱ የሶማሌ ክልል አካባቢዎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

165

ጥር 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) የደቡብ ክልል በድርቅ ለተጎዱ የሶማሌ ክልል አካባቢዎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ከክልሉ መንግስት የተደረገውን ድጋፍ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት የሶማሌ ህዝብ ኢትዮጵያ ጸንታ እንድትቆይ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለ ህዝብ ነው።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሁሉን አቀፍ እና ጠንካራ የአስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት በአስተሳሰብ የላቀ አመራር መፍጠር መቻሉን በአብነት ጠቅሰዋል።

በተፈጥሮ ድርቅ ባጋጠመው አደጋ የክልሉ መንግስት አለኝታነቱን ለመግለጽ ለመጀመሪያ ዙር 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት እና 15 ሚሊየን ብር በድምሩ የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቁመዋል።

የሁለቱን ክልል ህዝቦች ትስስር ለማጠናከር እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በበኩላቸው የደቡብ ክልል ያጋጠመንን ችግር በመረዳት ላደረገልን ድጋፍ ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ካለው ውስን ሀብት ቀንሶ ያደረገልን ድጋፍ በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል ሲሉም ጠቁመዋል።

በዝናብ እጦት ምክንያት ያጋጠመን አደጋ ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ሙስጠፌ ይህንንም ለመቋቋም ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተደረገ ነው ሲሉ መናገራቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼