“የጥምቀትን በዓል ስናከብር ከክርስቶስ የተማርነውን ለጋስነት በተግባር በማሳየት መሆን አለበት”

156

ጥቅምት 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) “የጥምቀትን በዓል ስናከብር ከክርስቶስ የተማርነውን ለጋስነት በተግባር በማሳየት መሆን አለበት” ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቴሌቪዥን ጣቢያ የበላይ ጠባቂ ብጹዕ አቡነ ማቲዎስ አሳሰቡ፡፡

የጥምቀት በዓል 44 ታቦታት በአንድ ላይ ሆነው በምንጃር ሸንኮራ ኢራንቡቲ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቴሌቪዥን የበላይ ጠባቂ ብጹዕ አቡነ ማቲዎስ፣ ባስተላለፉት መልእክት የጥምቀት በዓል የሰው ልጆችን የሀጥያት ደብዳቤ በመቅደድ ከባርነት ነጻ ያወጣበት መሆኑን ገልጸዋል።

ክርስቶስ የሰው ልጆችን ከዳቢሎስ እስር ነጻ ያወጣበት መንገድ ለሰው ልጆች መከባበርና መታዘዝን ያስተማረበት እንደሆነም ተናግረዋል።

በመሆኑም የጥምቀት በዓልን ስናከብር ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ከክርስቶስ የተማርነውን ለጋስነት በተግባር በማሳየት መሆን አለበት ብለዋል።

ለሀገር ሰላም መጸለይና ለተግባራዊነቱ መትጋት ያስፈልጋል ያሉት ብጹዕ አቡነ ማቲዎስ፤ ሰላም ከሌለ እንስሳትም ሆኑ የሰው ልጆች መኖር አይችሉምና ለሰላም ዘብ እንቁም ብለዋል።

የኢትዮጵያን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥም የተጀመሩ ስራዎችን ከግብ እንዲደርሱ የሁላችንም ተሳትፎ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼