ኢትዮጵያ በታሪክም በባህልም የተለየች ድንቅ አገር መሆኗን አይቻለሁ-ጣሊያናዊ ፎቶግራፈር

226

ጥር 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) “በጥምቀት ክብረ በዓል ታድሜ ኢትዮጵያ በታሪክም በባህልም የተለየች ድንቅ አገር መሆኗን አይቻለሁ” ሲል ጣሊያናዊ ፎቶግራፈር ጃኮፖ ብሮጊኒ ተናገረ።

ጃኮቦ ብሮጊዮኒ ጣሊያናዊ ዓለም አቀፍ ፎቶ አንሺ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ይላል።

ኢትዮጵያ ጥንታዊት በታሪክና በባህል የበለጸገች አገር መሆኗን በታሪክ ባውቅም፤ በአካል ተገኝቼ በጥምቀት ክብረ በዓል መታደሜ ግን ልዩ ስሜት ፈጥሮብኛል ብሏል።

የጥምቀት ክብረ በዓል የሚከበርበት ስርዓት፣ ለባህልና ስርዓቱ የሚሰጠው ክብር በእርግጥም ኢትዮጵያ ልዩ አገርና ልዩ ህዝብ ያላት አገር መሆኗን አረጋግጫለሁ ነው የሚለው።

ኢትዮጵያ አየሯ ተስማሚ፣ ሁሉን መልክዓ ምድራዊ ገጾች ያቀፈች ድንቅ አገር መሆኗንም በተግባር አረጋግጫለሁ ሲል ተናግሯል።

ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ወደ አስገራሚዋ አገር መጥተው ደስታቸውን እንዲያጣጥሙ በማለትም መልእክቱን አስተላልፏል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼