የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሚሊሻ ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

180

አምቦ፣ ጥር 10 ቀን 2014( ኢዜአ) የአምቦ ዩኒቨርሲቲ በከተማው ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅ ላይ ለሚገኙ 75 የሚሊሻ ቤተሰቦች የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የምግብ ሸቀጥ ድጋፍ አደረገ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር ባይሳ ለታ እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ድጋፉን ለማድረግ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል።

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃጫሉ ገመቹ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ጊዜ የአቅም ውስንነት ያለባቸውን ወገኖች ሲደግፍ መቆየቱን ገልጸው፤ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ሚሊሻዎቹ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር የአከባቢውን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅ ሕዝብና መንግሥት የሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው ሚሊሻዎች ዩኒቨርስቲውን አመስግነው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በቁርጠኝነት እንደሚወጡ አረጋግጠረዋል፡፡