የኢትዮጵያ መንግስት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘ

113

ጥር 10 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ መንግስት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሲቪል ተቋማት ላይ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አውግዟል።

የሽብር ጥቃቱ በየትኛውም የሰብአዊነት መመዘኛም ሆነ በአለም አቀፍ ህግ ሊወገዝ የሚገባው ድርጊት በመሆኑ ኢትዮጵያ በፅኑ ታወግዛለች ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ በጥቃቱ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ሞትና የአካል ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፤ለቆሰሉት ዜጎችም ፈጣን ማገገም ተመኝቷል።

ኢትዮጵያ ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስትና ህዝብ መጽናናትን እንደምትመኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም