ኢዜአ አገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሚያከናውናቸው ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው -ኮሚቴው

58

ድሬዳዋ ፤ ጥር 9 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) አገራዊ ለውጡን ለማስቀጠልና የህዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የሚያከናውናቸው ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስገነዘበ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና የዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በምስራቅ ተጎራባች ክልሎች የሚገኙ የፌደራል የህግና የዴሞክራሲ ተቋማትን የሥራ እንቅስቃሴ  እየገመገሙ  ይገኛሉ፡፡

በግምገማውም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  የሥራ እንቅስቃሴዎች  ተመልክቷል ፡፡

 የቋሚ ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ኢያሱ ሣላ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ኢዜአ በማእከልና በቅርንጫፎቹ በኩል ተአማኒ፣ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማድረስ አገራዊ ለውጡን ለማጠናከር እያከናወነ ያለው ተግባር አበረታች  ነው፡፡

ተቋሙ በቅርንጫፎቹ በኩል የህዝብን መሠረታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች  ምላሽ እንዲያገኙ የሚሰራቸው ዘገባዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ጠቁመው  "ተቋሙ በቀጣይ ሙያዊ ሥነ ምግባርን በማጽናት ታአማኒነትን ይበልጥ ለማሳደግ  በትኩረት መስራት ይገባዋል" ብለዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ከመሌ ጋዲሳ በበኩላቸው ኢዜአ በቅርንጫፍቹ በሚገኙ ጥቂት የሰው ኃይል  አማካኝነት በክልሎች የሚያከናወኑ ዋና ዋና የልማትና የሰላም ተግባራት እንዲሳኩ በማገዝ በኩል ሚናው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋሙ ክልሎችን የማገዝ ተግባሩን አጠናክተሮ ለመቀጠል ቅርንጫፎቹን በሰው ኃይል፣ በሥልጠናና በዘመናዊ ካሜራዎች ሊያደራጅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ፣የህግ፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ  ተመሳሳይ ግምገማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም