ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ተወያዩ

268

ጥር 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ውይይት አደረጉ።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የነበራቸው ውይይት በአገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ኢትዮጵያ እንደ ካናዳ ያሉ በሁኔታዎች የማይቀያየሩና ድጋፍ የሚያደርጉ ወዳጆች አክብሮት አላት” ብለዋል።

ኢትዮጵያና ካናዳ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1965 ነው።