የጤናማ እናትነት ወር በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰመራ ከተማ እየተከበረ ነው

210

ሰመራ ፤ ጥር 7/2014(ኢዜአ) ” ከወሊድ በኋላ በሚከሰት የደም መፍሰስ ምክንያት የእናቶች ሞት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንግታ ” በሚል መሪ ሀሳብ የጤናማ እናትነት ወር በሀገር አቀፍ ደረጃ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተከበረ ነው።
 
በመርሃ ግብሩ በደም መፍሰስና ተያያዥ ምክንያቶች የሚከሰቱ የእናቶች ሞት ለመቀነስ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አጋር አካላት እንዲሁም ከክልል እስከ ወረዳ የሚገኙ የፖለቲካ  አመራሮች የድርሻቸውን መወጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

የዱብቲ ሆስፒታል  በተለይም ለእናቶችና ህጻናት የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት እንቅስቃሴ  ጉብኝት እንደሚካሄድ ታውቋል።

በሀገር  ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ እየተከበረ በሚገኘው የጤናማ እናቶች ወር መርሃ ግብር ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰን ጨምሮ ሌሎችም  የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የጤናማ እናቶች ወር በየዓመቱ ጥር ላይ   በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ተመልክቷል።