በአገር አቀፍ ደረጃ ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል

113

ጥር 06ቀን 2014ዓ.ም(ኢዜአ) "ጥምቀትን በጎንደር" የተሰኘው ሀገራዊ የጥምቀት በዓል አከባበርና የዳያስፖራዎች መርሐግብር ዝግጅት መጠናቀቁን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መገለጫ ወደ አገር ቤት ለገቡ ዳያስፖራዎች የተዘጋጁ አገራዊ ሁነቶች በተያዘላቸው ጊዜ ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ የአደባባይ በዓላት መካከል በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው ጥምቀት ክብረ በዓል በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እንደሚከበር አውስተው "ዳያስፖራው ከሚሳተፍባቸው አገራዊ መርሐግብሮች መካከል አንዱ 'ጥምቀትን በጎንደር' የፊታችን ጥር 11 ይከናወናል" ብለዋል።

በመርሐግብሩ ሲምፖዚየም፣ ባዛሮች፣ የኪነ ጥበብ ምሽቶችና ሌሎች መድረኮች ይካሄዳሉ ነው ያሉት።

በጎንደር ዝግጅቱ መጠናቀቁንና በቀን እስከ 4 የአውሮፕላን በረራ እየተደረገ ስለመሆኑንም ገልፀዋል።

ይህም በኮቪድና ግጭት ምክንያት የተቀዛቀውን ቱሪዝም ዘርፍ እንደሚያነቃቃ ተናግረዋው የዳያስፖራው ወደ አገር ቤት መምጣት በተለይ ቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት መልካም ዕድል ስለመፍጠሩም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም