ከዳያስፖራዎች ጋር ያደረግነው ምክክር የቴክኖሎጂና የልምድ ክፍተቶችን ለመሙላት ያግዘናል

94

አዲስ አበባ ፣ ጥር 05/2014(ኢዜአ)   ከዳያስፖራዎች ጋር ያደረግነው ምክክር ያሉብንን የቴክኖሎጂና የልምድ ክፍተቶች ለመሙላት ያግዘናል ሲሉ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ገለጹ።

የምክክር መድረኩ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችና ዳያስፖራው ትስስር የሚፈጥሩበት መሆኑም ተገልጿል።

የምክክር መድረኩ ዓላማ ዳያስፖራዎች ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች ልምድና እውቀታቸውን እንዲያካፍሉ ማድረግ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል።

የተፈጠረው ትስስርም የዳያስፖራ አባላቱ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች ልምዳቸውን በማካፈል አገራዊ የልማት ስራውን ለማገዝ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

"ወቅቱ አገርን ተባብረን ወደ ላቀ ደረጃ የምናሸጋግርበት ነው" ያሉት ሚኒስትሯ መንግስት አስፈላጊ ሕጎችን በማዘጋጀት ለውጤታማነት የሚያበቁ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ወጣት ስራ ፈጣሪዎችም መድረኩ የተለያየ ልምድ ካላቸው ወገኖች ጋር ትስስር በመፍጠር ያሉብንን የቴክኖሎጂና የልምድ ክፍተቶች ለመሙላት ያግዘናል ብለዋል፡፡

ከተለያዩ የዓለም አገራት የመጡ የዲያስፖራ አባላትም በየትኛውም ዘርፍ አገር ለምታደርገው ጥሪ ግንባር ቀደም ሆነው ለመገኘት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ያሉባቸውን የልምድ፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ክፍተቶች ለመሙላትና የሚጠበቅባቸውን እገዛ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነትም አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም