የዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው

ሀዋሳ፤ ጥር 1/2014 (ኢዜአ) በደቡብ ክልል የሀላባ ብሔር የዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በቁሊቶ ከተማ እየተከበረ እገኛል።
በዓሉ እየተከበረ ያለው በሲምፖዝየም ሲሆን የብሔሩ ባህላዊ አስተዳደር መተዳደሪያ ደንብ የሆነውን ሴራን መሰረት አድርጎ የሚከበር እንደሆነ ተጠቁሟል።
በዘመን መለወጫ በዓሉ ላይ የዞኑና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከየወረዳው የተውጣጡ የብሔሩ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
የሴራ በዓል በወረዳ ደረጃ በየዓመቱና በዞን ደረጃ ደግሞ በየሁለት ዓመቱ የሚከበር ነው።